Print
Category: ase
Hits: 233

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲንና ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ፈጣንና ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ምርጥ ዘርን በባለቤትነት አምርቶና አዘጋጅቶ የሚያቀርብ ራሱን የቻለ ተቋም መፍጠር ማስፈለጉን ተከትሎ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዝክረ-ሕግ ደንብ ቁጥር 66/2001 ግንቦት 28 ቀን 2001 ዓ.ም የተቋቋመ የልማት ድርጅት ነው፡፡

የምርጥ ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ማዕከላት መሰረታዊ መረጃ

 

ብርሸለቆ ምርጥ ዘር ብዜት ጣቢያ የተቋቋመበት ዓ.ም 2010

የኢንተርፕራይዙ ዓላማዎች

 የኢንተርፕራይዙ ራዕይ

የአማራ ክልል አርሶ አደሮችንና በግብርና ዘርፍ የተሰማራውን ባለሃብት የዘር ፍላጐት በማሟላት ወደ ኢንዱስትሪው ዕድገት ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት እገዛ የሚያደርግ እና በዘር ኢንዱስትሪው በክልልም ሆነ አገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጠንካራ የሆነ የዘር ኢንተርፕራይዝ ተፈጥሮ ማየት

የኢንተርፕራይዙ ተልዕኮ

ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እና የእንስሳት መኖ ዘሮችንና ችግኞችን ከተለያዩ ምርምር ማዕከላትና ከውጭ ሃገር በመግዛትና በማስገባት ሳይንሳዊ የአመራረት ሥርዓትን ተከትሎ በማምረትና በማዘጋጀት ለክልሉ አርሶ አደሮችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ማቅረብ

የኢንተርፕራይዙ እሴቶች